የቤተሰብ ነክ ዘርፍ
በ Immigration and Refugee Protection Act መመርያ መሰረት፥ የካናዳ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪዎቹ (Canadian citizens and Canadian permanent residents) ፥ ባለትዳሮቻቸውን ፥ ከ22 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉት ልጆቻቸውን፥ በጣም በተወሰነ መልኩ ደግሞ፥ ወንድ ኣያትና ሴት ኣያት እንዲሁም ዘመድን ስፖንሶር ለማድረግ፥ መንገድ ይከፍትላቸዋል። እያንዳንዱ የዚህ ቤተሰብ-ነክ ዘርፍ ማመልከቻ፥ ኣመልካቹ ለፕሮግራሙ ብቁ ነው ኣይደለም ለማለት የሚያስወስነው መመዘኛና ትርጓሜ የያዘ ነው። በቤተሰብ-ነክ ዘርፍ ባሉት ንዑስ ዘርፎች፥ ከ12 ዓመታት በላይ የስራ ልምድ ኣለን። እዚሁ ድረ-ገጻችን ላይ ያሰፈርነው፥ ከቤተሰብ-ነክ ዘርፍ ስር ከፍተኛው ድርሻ የያዘውን ነው።
ባለ ትዳሮችን ስፖንሶር (የማስመጣት) ማመልከቻ ሒደት
የካናዳ ዜጐችና የካናዳ ቋሚ ነዋሪዎች፥ የትዳር ኣጋሮቻቸው እዚሁ ካናዳ ቋሚ ነዋሪዎች እንዲሆኑ፥ ማመልከቻ (application) የማቅረብ መብት ኣላቸው። ይሁንና፥ ስፖንሶር የሚደረግ ሰው፥ የቋሚ ነዋሪነትን ቪዛ ለመቀበል፥ የግድ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶችን፥ ያሟላል ወይም ኣያሟላም፥ መታወቅ ኣለበት። በተጨማሪ፥ ወደ ካናዳ ለመግባት የሚያግደው ነገር ኣለ ወይስ የለም የሚለው ጥያቄ፥ ተገቢው መልስ ማግኘት መቻል ኣለበት። ልክ እንደ ሌሎቹ ኣያሌ የኢሚግረሽን ዘርፎች፥ የትዳር ኣጋርን ስፖንሶር ለማድረግ፥ ቪዛ የሚፈቅደው የኢሚግረሽን ኦፊሰሩ ነው። ኣብዛኛው ጊዜ፥ እንደ ምሳሌም የሚጠቀሰው፥ ኢሚግረሽን ኦፊሰሩ፥ ባልን ወይንም ሚስትን ስፖንሶር ለማድረግ የሚቀርብለትን ማመልከቻ፥ ዉድቅ የሚያደርግበት ምክንያት፥ የተፈጸመው ጋብቻ እውነትነት ያለውና በቅን ልቦና የተደረገ ሳይሆን፥ ኣመልካቹን ወደ ካናዳ ለማስመጣት ብቻ ያነጣጠረ ዓላማ ያለው ነው ብሎ በሚያምንበት ሁኔታ ነው። ዉድቅ የተደረገ ማመልከቻ ከመቀበልና፥ በማመልከቻ ሒደት ላይ ከሚያጋጥመው መዘግየት ለመዳን፥ ማመልከቻው ላይ የተጠየቀውን ኣስፈላጊና ዝርዝር መረጃ፥ እንዲሁም ይኸንኑ የሚደግፉ ሰነዶችን ኣሟልቶ ማቅረብ የግድ ይላል። ባለ ትዳርዎን ስፖንሶር ማድረግ ከፈለጉ፥ ጠይቁን በደስታ እናስተናግዳችኋለን።
ለዓቅመ-ኣዳም / ዓቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ልጆች ስፖንሶር ማድረግያ ዘርፍ
ዕድሚያቸው ከ22 ዓመት ያነሰና ያላገቡት ልጆች፥ የካናዳ ዜጎች/ ቋሚ ነዋሪዎች በሆኑ ወላጆቻቸው፥ ስፖንሶር ለመሆን ይችላሉ። በተጠቀሰው የኢሚግረሽን ዘርፍ ቪዛ ለማግኘት፥ ስፖንሶር በሚያደርገው ወላጅና፥ ስፖንሶር በሚደረገው ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ማስመስከርና፥ ልጁ ወደ ካናዳ ለመግባት የሚያግደው ነገር እንዳይኖር የሚጠይቀውን መስፈርት፥ (admissibility requirements) ማሟላት መቻል ኣለበት። ልጅዎን ስፖንሶር ለማድረግ፥ ሙያዊ ኣገልግሎት ካስፈለግዎ፥ ያግኙን።
ወላጅ-ኣልባ ዘመድ
በዚህ ቤተሰብ-ነክ ዘርፍ በወጣው መመርያ መሰረት፥ የካናዳ ዜጐችና ቋሚ ነዋሪዎች፥ ወንድሞቻቸውን፥ እህቶቻቸውን፥ የወንድሞቻቸውና የእህቶቻቸውን ልጆች፥ ዕድሚያቸው ከ 18 በታች እስከሆነና፥ ስፖንሶር የሚያደርገው ሰው ደግሞ፥ ገቢውን በሚመለከት ቢያንስ ቢያንስ ማሟላት የሚገባውን የገቢ መመዘኛ (minimum income requirements) እና ስፖንሶር ለማድረግ መሟላት የሚገባቸውን ነገሮች እስካሟሉ ድረስ፥ በወላጅ-ኣልባ ዘመድ ዘርፍ ስር ማመልከት ይችላሉ። ኣንድ ሰው እንደ ወላጅ-ኣልባ ለመቆጠር፥ ሁለቱም ወላጆች፥ መሞታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የግድ ይላል። ወላጅ-ኣልባ የሆነን ዘመድዎ፥ ስፖንሶር ለማድረግ ካስፈለግዎ፥ ይኸንኑ የግምገማ ቅጽ ይምሉት።
ሌሎች ዘመዶች (ብብቸኝነት የሚብሰለሰል ካናዳዊ)
የካናዳ ዜጐችና ቋሚ ነዋሪዎች፥ ስፖንሶር በሚያደርጉበት ወቅት ምንም ይሁን ምን፥ ስፖንሰሩ በሕይወት ያለ ባለ ትዳር፥ ልጅ፥ ወንድ ኣያት ወይም ሴት ኣያት፥ ወላጅ-ኣልባ ወንድም ወይም እህት፥ እና የልጅ ልጅ የሌለው እንደሆነ፥ ማንኛውንም ሌላ ዘመድ ስፖንሶር ማድረግ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ፥ ስፖንሰሩ ማንኛውም እዚሁ ካናዳ የካናዳ ዜግነት ወይም ቋሚ ነዋሪነት ያለው ዘመድ (ኣክስት፥ ኣጐት ወይም ሌላ ማንኛውም እዚህ እንደ ዘመድ ከተዘረዘሩትም ቢሆን) ሊኖረው ኣይገባም ። ለተጨማሪ መረጃ እኛን ያግኙን።
ስደተኛን ስፖንሶር ማድረግ
ስደተኞችን በግል ስፖንሶር ማድረግና (private sponsorship of refugees, abbreviated as ‘PSR’) ፥ ስደተኞችን በመንግስት በኩል ስፖንሶር ማድረግ (government assisted refugees, abbreviated as GARS) ፥ ከካናዳ ዉጪ ያሉትን ስደተኞች፥ ወደ ካናዳ እንደ ቋሚ ነዋሪዎች ሆነው እንዲመጡ የሚያስችል፥ በ Refugee and Humanitarian Resettlement Program የሚተዳደር ዘርፍ ነው። ስደተኞችን በግል ስፖንሶር ማድረግን በሚመለከት፥ Private Sponsorship of Refugees: ስፖንሰሮቹ፥ ስደተኛው በኑሮው እንዲቋቋም የሚያስፈልግ ድጋፍ ለመጀመርያዎቹ 12 ወራት ወይም ደግሞ ስደተኛው ራሱን እስኪችል ድረስ፥ ከሁለቱም ቀድሞ የተከሰተውን በመውሰድ፥ ድጋፍ የሚሰጡ መሆናቸውን ቃል ይገባሉ። ካናዳ፥ ስደተኞችን በግል ስፖንሰሮች በኩል ስፖንሶር በማድረግ ኣሰራር ፈር ቀዳጅ ኣገር ነች። ድርጅታችን፥ በዚሁ በስደተኞች ስፖንሶር ስራ ከ 12 ዓመታት በላይ ልምድና የተካነ ዓቅም ኣለው። ድርጅታችን፥ ስደተኞችን ስፖንሶር ለሚያደርጉ ሰዎች፥ በተለይም 5 ኣባላት ያሉትን ቡድን፥ እንዲሁም በኮሚዩኒቲ ፕሮግራም (Group of Five and community sponsorship streams) ያሉትን ደንበኞች፥ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል።
የቡድን 5 ፕሮግራም
ይኸው ፕሮግራም ፥ ኣምስት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የካናዳ ዜጎች ወይም ቋሚ ነዋሪዎች፥ ዉጭ ኣገር ያለውን ስደተኛ፥ ወደ ካናዳ ኣስመጥተው፥ ኑሮውን እንዲቋቋም የሚረዱት መሆኑን፥ ከካናዳ መንግስት ጋር ዉል የሚገቡበት፥ በግል ስፖንሶር በሚሆኑት ስደተኞች ስር ያለ ንዑስ ክፍል ነው። ይኸው ፕሮግራም የሚከናወነው፥ እነዚህ ስፖንሰሮች፥ ከስደተኛው ቤተሰብ ቁጥር በተጣጣመ መልኩ፥ ስደተኛው ኑሮውን እንዲያሸንፍ የሚረዳ በቂ የመቋቋሚያ ዕቅድ ያላቸው መሆኑን፥ በጽሕፈት ቤት ቅጾች ላይ ካሳዩ ነው። እነዚህ የቡድኑ ኣባላት፥ ስደተኛውን ወይንም የቤተሰቡን ኣባላት፥ ለ12 ወራት ወይም ደግሞ ስደተኛው ራሱ እስኪችል ድረስ፥ ቀድሞ የተከሰተውን በመውሰድ፥ ከገቢያቸው ኣኳያ ቃል ሊገቡ፥ ወይንም ደግሞ ገንዘቡን ከተለያዩ በጐ ኣድራጊዎች ሊሰበስቡ ይችላሉ። እነዚህ ፎርሞችን መሙላት፥ ቀላል ሊመስል ይችል ይሆናል። ይሁንና፥ በየጊዜው የሚቀያየሩት መመርያዎች፥ ሰነድን የሚመለከቱ ጉዳዮች (documentation) እንዲሁም፥ ሒደቱ እንዲሟሉ የሚጠይቃቸው ነገሮች፥ ትኩረት የሚሹ፥ ጥቃቅን ቢሆንም ጥንቃቄ የሚጠይቁ ነገሮች ስላሉ፥ ስራው ከፍተኛ ማስተዋልና ሞያዊ ብቃትን ይጠይቃል። በዚህ ፕሮግራም ስር፥ ስደተኛን ስፖንሶር ማድረግ ከፈለጉ፥ የመጀመርያ ግምገማ preliminary assessment: ለማግኘት፥ ያግኙን።
ስፖንሶር በኮሚዩኒቲ
የተቋቋመና ያልተቋቋመ ንግድ ወይም ማህበርን (an incorporated and unincorporated business or association) ይመለከታል። ይኸው ድርጅት፥ ስደተኛውን የገባለት ቃል ለሟሟላት፥ የገንዘብና ፥ ስደተኛው ኑሮውን ለመቋቋም የሚያስችል ዓቅም ያለው ሆኖ፥ የሚኖርበት ቦታ ስደተኛው ይኖርበታል ተብሎ የሚታሰብበት ቦታ ላይ መሆን ኣለበት። የኮሙኒቲ ስፖንሶሮች፥ ማመልከቻው ላይ የተጠየቀውን ኣስፈላጊ መረጃና፥ ይኸንኑ የሚደግፉ ሰነዶችን ኣሟልቶ ማቅረብ፥ የግድ ይላል። የኮሙኒቲ ስፖንሰሮች፥ እነዚህን ዓቅሞች እንዳሏዋቸውና፥ ስደተኞችን ሞራላዊ እና ማህበራዊ ድጋፎች እንደሚሰጧቸው፥ እስከ ተጠየቀው ጊዜ ድረስ ዕገዛ የሚያደርጉላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ የግድ ነው።
ኣንድ ስደተኛ፥ በግል ስፖንሶሮች ወይም በኮሚዩኒቲ በኩል ስፖንሶር ለመደረግ የሚያበቃ መስፈርት፥ ማለትም ዋና ኣመልካቹ (ስደተኛው)፥ ማመልከቻውን ወደ Immigration Canada ከመላኩ በፊት፥ የስደተኝነትን ተገን ጠይቆ ስደተኛ መሆኑ /full refugee status/ የተመሰከረለት፥ ይኸንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዲኖረው፥ ያስፈልጋል። ይህ ማለት ይኸንኑ ጉዳይ ለመወሰን ስልጣን ያለው ኣካል፥ ኣመልካቹ ስደተኛ ነው ተብሎ የቀረበለት ምክንያት ኣሳምኖታል ማለት ነው። ይህ ስልጣን ያለው ኣካል፥ UNHCR (የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር) ወይም ደግሞ ስደተኛው እየኖረ ባለበት ፥ የኣንድ ሉኣላዊት ኣገር መንግስት (የዉጭ ኣገር መንግስት) ሊሆን ይችላል። ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፥ በቡድን 5 (Group of Five) ኣማካኝነት፥ የስደተኛ ከለላ የሚጠይቁትን ሰዎች (asylum seekers) ስፖንሶር ማድረግ ኣይቻልም። ይሁንና፥ ኣንድ የስደተኛ ከለላ ጠያቂ፥ ከኣንድ ስደተኛ መሆኑ ከተመሰከረለት (full status ) ካለው ሰው ጋር በትዳር የተጣመረ የሆነ እንደሆነ፥ ኣብሮ ስፖንሶር ሊደረግ ይችላል።
የካናዳ ኢሚግረሽንና ስደተኞች ቦርድ ችሎት ተግባር
የካናዳ ኢሚግረሽንና ስደተኞች ቦርድ IRB (Immigration and Refugee Board of Canada) በኢሚግረሽንና ስደተኛ ጉዳይ ላይ፥ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው ኣካል ሆኖ፥ ተግባራቱን በኣራት መንገዶች ያከናውናል። ይኸንኑ የሙያዊ ኣገልግሎት ማቅረብ ከጀመርንበት ግዜ ጀምሮ፥ ኣቶ ተወልደ ዮሐንስ፥ እንደነ ባለትዳሮችን ስፖንሶር ማድረግ (sponsorship): ባለትዳርን ስፖንሶር ከማድረግ ጋር የሚያያዙትን የይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ፥ ለስደተኛ ተገን ጠያቂዎችና መጤዎች (asylum seekers and immigrants) ስኬታማ የሆነ የኣገልግሎት ውክልና ሲሰጡ ቆይተዋል።
የስደተኛነት ተገን ማመልከቻ የሚቀርብበትና ይግባኝ የሚጠየቅበት
ሰዎች ባላቸው ዘር፥ ሃይማኖት፥ ማንነት፥ የፖለቲካ ዕይታ ወይም የኣንድ የተወሰነ ማህበራዊ ቡድን ኣባል በመሆናቸው ምክንያት እየታደኑ በመሆናቸው፥ ስር የሰደደ ፍርሓት ያደረባቸው የዉጭ ዜጐች፥ የስደተኝነትን ተገን (ከለላ) እንዲሰጣቸው፥ ማመልከቻ ለማቅረብ ይችላሉ:: የስደተኛነት ተገን (ከለላ) የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ፥ በሕይወታቸው ላይ ያጋጠማቸው ኣደጋ ወይ ሰቆቃ፥ በጨካኝና ባልተለመደ ኣኳኋን ያለፉ፥ ከመጡበት ኣገር ቅጣት የሚወርድባቸው መሆኑን፥ በብቁ ሁኔታ ማስመስከር ከቻሉ፥ ካናዳ የስደተኝነት ተገንን ትሰጣቸዋለች። ካናዳ ውስጥ የስደተኝነት ተገን ጥያቄ ማመልከቻ፥ ኣመልካቹ መጀመርያ ካናዳ እግራቸው ያረፉበት መግቢያ (Port of Entry) ፡ ኣገር ውስጥ የሚገኝ የኢሚግረሽንና ስደተኞች ጽሕፈት ቤት (IRCC) ወይም ደግሞ፥ በካናዳ የድንበር ጥበቃ ኣገልግሎት ጽሕፈት ቤት (Canada Border Services Agency) በኩል ሊቀርብ ይችላል። የስደተኞች መብት ጥበቃ መምርያ (Refugee Protection Division) ፥ ካናዳ ውስጥ የሚቀርበውን የስደተኛ ተገንን የሚጠይቅ ማመልከቻ፥ በዓለም ኣቀፋዊ የጀነቭ ስምምነት መሰረት (International Geneva Convention) ጉዳዩን በመመርመር ዉሳኔ በመስጠት፥ በኢሚግረሽንና ስደተኞች ጥበቃ ኣዋጅ (Immigration and Refugee Protection Act) ተሞርኩዞ ተግባር ላይ ያውላል። ኣመልካቾቹ፥ ኣዎንታዊ (positive) ዉሳኔ ያገኙ የስደተኛ ተገን ጠያቂዎች፡ ተገን የተሰጣቸው ስደተኞች (protected persons) ወይም ተገን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ ሰዎች፥ የቋሚ ነዋሪነት ፍቃድ ሰነድ ለማመልከትም፥ ብቁ ይሆናሉ። ማመልከቻቸው፥ ዉድቅ የተደረገባቸው የስደተኛ ተገን ጠያቂዎች፥ ወደ ስደተኛ ይግባኝ ሰሚ መምርያ Refugee Appeal Division (RPD) ማመልከት ይችላሉ። የስደተኛ የይግባኝ መምርያው ደግሞ፥ የስደተኞች ጥበቃ መምርያ (Refugee Protection Division) የሰጠውን ዉሳኔ፥ እንዳለ ሊቀበለው ወይም ደግሞ ዉድቅ ሊያደርገው ይችላል። እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ ኣባል፥ የስደተኛ ተገን ጥያቄ ወይም ደግሞ የይግባኝ ማመልከቻ ለማቅረብ ካስፈለግዎ፥ ባለን ሙያዊ ብቃትና ልምድ መገልገል ይችላሉ።
ኢሚግረሽን የይግባኝ ማመልከቻ ማቅረብ
የኢሚግረሽን ይግባኝ ሰሚ መምርያ፥ ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡትን የኢሚግረሽን-ነክ የይግባኝ ጉዳዮችን፥ ችሎት ዘንድ የማዳመጥ ስልጣን ኣለው።
-
በኢሚግረሽን፥ ስደተኞችና ዜግነት ጽሕፈት ቤት (IRCC) እና በኤምባሲ ባሉት ባለስልጣኖች ዉድቅ የተደረጉ፥ የቤተሰብ-ነክ ስፖንሶርሺፕ፥ የይግባኝ ማመልከቻን በተመለከተ (ለምሳሌ የባለትዳሮች ስፖንሶርሺፕ ማመልከቻ ዉድቅ የተደረገባቸው)
-
ኣገርን ለቀው እንዲወጡ የተወሰነባቸው ቋሚ ነዋሪዎች፥ ተገን የተሰጣቸው ስደተኞችና የቋሚ ነዋሪነት ቪዛን የያዙ ሰዎች የይግባኝ ጉዳይ
-
ከካናዳ ዉጪ ባለው የኢሚግረሽን፥ ስደተኞችና ዜግነትን ጽሕፈት ቤት ባለስልጣን፥ ቋሚ ነዋሪዎች ማሟላት የሚገባቸውን በካናዳ የመኖር ግዴታ መስፈርት፥ ሳያሟሉ የቀሩ ቀዋሚ ነዋሪዎች የይግባኝ ጉዳይ
ኣንድ ስፖንሶር፥ በቤተሰብ-ነክ ዘርፍ በኩል የትዳር ኣጋርን ስፖንሶር ለማድረግ፡ ለቪዛ ቢሮ ያቀረቡትን ማመልከቻ ዉድቅ በተደረባቸው፥ በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ የይግባኝ ማመልከቻን ማቅረብ ይችላሉ። የኢሚግረሽን ይግባኝ ሰሚ መምርያ (Immigration Appeal Division) ዘንድ የሚታየው ጉዳይ፥ ተጻራሪ ኣቋም የሚስተናገድበት ሒደት ሆኖ፥ ኣብዛኛው ጊዜ ይግባኝ ባዩን በመቃወም፥ መከራከርያ የሚያቀርበው የሚኒስትሩ ጠበቃ ነው። የካናዳ ኢሚግረሽንን ስደተኛታት ቦርድ IRB (Immigration and Refugee Board of Canada): ኣባል፥ የቀረበውን የቃል ምስክርነትና በሰነድ የተረጋገጠውን ማስረጃ በማመዛዘን፥ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ኣለው። ያቀረቡት የቤተሰብ ማመልከቻ (Family class sponsorship application) ዉድቅ የተደረገብዎት ከሆነ፡ ወይም ደግሞ ጉዳይዎ ወደ የይግባኝ ሰሚ ችሎት የመሔድ ኣዝማሚያ ያያዘ እንደሆነ፡ ሒደቱ ላይ እርስዎን ወክለን፡ ሞያዊ ኣገልግሎት ለመሰጠት እንችላለን።
ጎብኝዎች እና
የጊዝያዊ የመኖርያ ፍቃድ
በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የዉጭ ዜጎች፥ እንደ ኣገር ጐብኚዎች፥ ተማሪዎችና ጊዚያዊ የዉጭ ኣገር ሰራተኖች (Temporary Foreign Workers) በመሆን ወደ ካናዳ ይመጣሉ። ድርጅታችን፥ ከመላው ዓለም ካናዳን ለመጐብኘት፥ በካናዳ ለመማርና፥ የስራ ፈቃድን ለማግኘት የሚፈልጉ የዉጭ ዜጎች፥ የሚያስፈልጋቸውን ማመልከቻ (application)፥ በተሟላ መልኩ ኣጠናቀው፡ እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸውን ዓቅም ገንብቷል።
ለወላጆች፡ ለወንድ ኣያትና ለሴት ኣያት የሚሰጥ ሱፐርቪዛ
ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት፥ ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ ወላጆች፥ የወንድና ሴት ኣያቶችን ስፖንሶር የማድረግ ሒደት ብዙ ጊዜ ሲቀያያር ቆይቷል። ይሁንና ለዚሁ ዘርፍ ብቁ የሆኑ የካናዳ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪዎች ወላጆቻቸውን፥ በሱፐር ቪዛ (super visa) ዘርፍ በኩል፥ መጋበዝ ይችላሉ። ኣንድ ስፖንሶር፥ ቢያንስ ቢያንስ መሟላት ያለባቸውን ዝቅተኛ መስፈርቶችን (እዚሁ link ይጫኑ) እስካሟላ ድረስ፥ ወላጆችን ለማስመጣት በንጽጽር ሲታይ፥ የተቀላጠፈና በገንዘብም በኩል ረከስ ያለ መንገድ ነው። ኣንድ ወላጅ በዚሁ ፕሮግራም / ዘርፍ ስር፥ የጐብኚ ቪዛ ካገኙ፥ ዓይነተኛ ወይም የተለመደው ሊባል በሚችለው መልኩ፥ ብዙ ጊዜ ገብተው ለመውጣት የሚያስችላቸውን ቪዛ (multiple entry visa) ፥ የፓስፖርታቸው ጊዜ እስኪወድቅ ድረስ ወይንም ደግሞ ለኣስር ዓመታት፥ ከሁለቱ ጊዜያት ቀድሞ የተከሰተውን ጊዜ፥ ይሰጣቸዋል። ወላጆቹ፥ ኣንዴ ወደ ካናዳ ከመጡ፥ እስከ ሁለት ተከታታይ ዓመታት ድረስ፥ እዚሁ እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ከዚሁ በተጨማሪ፥ እንደ ጐብኚ ሆነው ለተጨማሪ ጊዜ እንዲቆዩ፥ የማራዘሚያ ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል። በዚሁ የሱፐር ቪዛ (super visa) ዘርፍ በኩል፥ ወላጆችዎን ለማስመጣት ከፈለጉ፥ ያግኙን።
ዜግነት
የካናዳ ዜግነት የሚሰጥበት
ቀዋሚ ነዋሪዎችን በሚመለከት፥ ምንም እንኳ ሕጋጋቱ ላይ የመኖር፥ የመስራትና የማጥናት (የመማርን) መብት የሚያሰጥ ቢሆንም፥ እነዚህ መብቶች በኣንዳንድ ሁኔታዎች ምክንያት ሊነጠቁ ይችላሉ። እነዚህ ሁኔታዎች፥ ለምሳሌ (proof of misrepresentation) እርስዎ ያልሆኑትን እንደሆኑ ኣስመስለው፡ ያገኙት ፈቃድ መሆኑ ማረጋገጫ ቢገኝብዎ፥ ወይም ደግሞ ከባድ ወንጀል ቢፈጽሙ፥ ወይም በኣምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ730 ቀናት በላይ በካናዳ ያልኖሩ ቢሆኑ ነው። ይሁንና፥ ካናዳዊ ዜጋ መሆን፡ የቀዋሚ ነዋሪነት ፈቃዱን ወይም ደግሞ የዜግነት መብቱን በዉሸት ማንነት (false representation) ላይ የተመሰረተ ወይም በማታለል (fraud) የተገኘ እስካልሆነ ድረስ፥ ከካናዳ ተገዶ ከመልቀቅ፥ ከሞላ ጐደል ነጻ (virtual immunity) የሚያደርግ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፥ የዜግነት መብት፥ ድምጽ የመስጠት፥ ጉዞ ለማድረግ የተሻለ ዕድልና ኣንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ያስችላል።
ቀዋሚ ነዋሪዎች፥ ኣንዴ በካናዳ መኖር የሚገባቸውን ጊዚያትንና የኖሩ እንደሆኑ፥ የቋንቋ መስፈርቶችን ያሟሉና የዜግነት ፈተና ያለፉ እንደሆነ፥ የካናዳ ዜግነት ለማግኘት ብቁ ናቸው። ድርጅታችን፥ እርስዎ ማቅረብ የሚጠበቅብዎት፥ ለካናዳ ዜግነት የሚያበቃ መስፈርትን ያሟሉ መሆኑን፥ እርስዎን በመወከል፡ የዉሳኔ ሰጪውን ኣካል በማሳመን ረገድ መርዳት ይችላል።
በኢሚግረሽንና ስደተኞች መብት ጥበቃ፥ (section A25(1) of the Immigration and Refugee Protection Act (IRPA) መሰረት፥ ወደ ካናዳ ለመግባት የሚያግዳቸው ነገር ቢኖር፡ ወይም ለቋሚ ነዋሪነት ለማመልከት ብቁ ባይሆኑም፡ ጉዳያቸው ሰብኣዊ ኣያያዝና ርህራሄ የሚሻ ጉዳይ ነው ብሎ በመውሰድ፡ ሕጉ የሚጠይቀው መመዘኛዎች ተነስተውላቸው፡ የቋሚ መኖርያ ፍቃድ ለማግኘት እንዲያመለክቱ ይፈቀድላቸዋል። ከተለመደው ለየት ባለው ኣኳኋን፡ ኣመልካቹን የሚያጋጥመው መከራ፡ ከግምት በማስገባት፡ ወይም ልጆችን ይጠቅማል በሚል ታምኖበት፡ ኦፊሰሩ የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል። ማመልከቻው፡ ኣዎንታዊ መልስ የማግኘት ዕድሉ ከፍ ይል ዘንድ፡ በማመልከቻው ኣሞላል ላይ የግድ ኣስፈላጊ የሆኑ ነገሮችና እነሱን የሚመለከቱ መርሖዎች በተመለከተ ጠለቅ ያለ ዕውቀትን ማዳበር፡ በየጊዜው የሚወጡ ፍርድ ቤቶች ቀደም ብለው ዉሳኔ የሰጡባቸውን ኣሳማኝ ኣዳዲስ ጉዳዮች (Case law) ላይ ተመርኩዘው የሚወጡ ሕጎችን በጥልቀት ማወቅን ይጠይቃል።