ወደ መጪው ጊዜ መኖርያ ቦታዎ ያቅኑ
በኢሚግሬሽን እና በስደተኛ ህግ ለ12 ዓመታት በሥራ የዳበረ ልምድ
በዕውቀትና ክህሎት ላይ ተመስርቶ ተግባራዊ ምክሮችን እና ውክልናዎችን ለመስጠት የተቋቋመ የካናዳ የኢሚግሬሽን እና የስደተኞች ህግ አማካሪ ድርጅት
ራዕያችንና ተልዕኮኣችን
ራዕያችን ሙያዊ ዕውቀት፥ ብቃት፥ ጥበብና ቅንነት የተላበሰች፥ ለደንበኞቻችን በሚመች መልኩ፡ የላቀ ኣገልግሎት የምታቀርብ፡ ከተለያዩ ዳራ የመጡት ደንበኞቿ፡ ዝናዋን የሚያስተጋቡላት ድርጅት እንድንሆን ነው። ተልዕኮኣችን፡ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ መልኩ በሚተገበር፡ ደንበኞቻችን በሚገባቸው ኣኳኋን፡ ሙያዊ የምክር ኣገልግሎትና ዉክልና፡ ለማቅረብ ነው። የድርጅታችን ስም እንደሚያመላክተው፡ ሰብኣዊነትን የሚያንጸባርቅ፥ እንክብካቤና ትጋት በሚያስተናግደው ኣቀራረብ፥ ደንበኞቻችንን ኣገልግሎት መስጠት ነው።
ስልታችን
ኣሰራራችን፡ የእያንዳንዱ ደንበኛ ፍላጐትና ምርጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት፡ ደንበኛ-ተኮር (customized service) ኣገልግሎት መስጠት ነው። ኣንዱ ደንበኛ ሌላው ደንበኛ ከሚያስፈልገው ሞያዊ የዕገዛ ዓይነት እና መጠን ይለያያል። በመሆኑም፡ እላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በማስተዋል፡ 3 የኣገልግሎት ደረጃዎች ማለትም i) የምክር (consultation) ኣገልግሎት 2) ዳግም የማየት / የመመርመር ኣገልግሎት (application review) 3) የሙሉ ውክልና ኣገልግሎት (full representation) ፡ ሌሎች የኛን ያህል ልምድና ዕውቀት ያላቸው ድርጅቶች፡ ለተመሳሳይ ኣገልግሎት ከሚጠይቁት ክፍያ ጋር፡ ተወዳዳሪ በሆነ ዋጋ፥ ከፍተኛ ደረጃ የያዘ ኣገልግሎትን እናቐርባለን።