![](https://static.wixstatic.com/media/7fc945_0eb15e5b0cb942da8192c9ff0635c309~mv2.jpg/v1/fill/w_1024,h_522,al_c,q_85,enc_avif,quality_auto/7fc945_0eb15e5b0cb942da8192c9ff0635c309~mv2.jpg)
የምክር ኣገልግሎት
![ADVICE_edited.jpg](https://static.wixstatic.com/media/7fc945_6eb40db03b294c8bb3d4e661b0c2402d~mv2.jpg/v1/fill/w_365,h_258,al_c,lg_1,q_80,enc_avif,quality_auto/ADVICE_edited.jpg)
በመጀመርያ ቀን ከደንበኞቻችን ጋር የምናደርጋቸው የምክክር ስብሰባ ላይ፥ ደንበኞቻችንን የሚያስፈልጋቸው ነገር በሚገባ ኣስተውለን እናዳምጣለን። ከዚያ በኋላ፥ ስላሉት የተለያዩ የኢሚግረሽን ዘርፎችና፥ ከነሱ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የማመልከቻ ሒደት (application process) እንገልጽላቸዋለን። ድርጅታችን ኣመልካቹ የሚፈልገውን የኢሚግረሽን ዘርፍ፥ ደንበኛውን ብቁ ሊያደርገው የሚችል መሆኑንና ኣለመሆኑን፥ ማመልከቻው ከተላከ በኋላ ሊኖረው የሚችለው የመጽደቕ ዕድል እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚጠየቁ ወጪዎች (cost) ይተነትናል። የዚህ ዓይነት ኣገልግሎት፥ ካልጋሪ ከሚገኘው ጽሕፈት ቤታችን በኣካል እና፥ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ዘንድ ከሚገኙት ደንበኞቻችን ጋርም፥ የመገናኛ ተክኖሎጂ ዘዴዎችን (virtually) በመጠቀም እንገናኛለን። ሙያዊ ኣገልግሎታችን ለማግኘት የሚፈልጉ ደንበኞቻችን፥ በስራ ሰዓታት 403 474 0342 ስልክ በመደወል፥ በድረ-ገጻችን የግልዎ መረጃዎችን ድሕንነት (Confidential) በሚጠብቀው፥ ‘ያግኙን’ (contact us) በተሰኘ ዓምዳችን፥ ልታገኙን ትችላላችሁ። ለምንሰጠው ማንኛዉም የኢሚግረሽን ኣገልግሎት፥ consultation fee (የምክክር ክፍያ) የምናስከፍል ቢሆንም፥ ኣገልግሎታችንን ለማግኘት ከኛ ጋር ተስማምተው የተዋዋሉትን ደንበኞች፥ ይኸው consultation fee (የምክክር ክፍያ) ፥ ሙሉውን የኣገልግሎት ዉክልና (full representation) ለመክፈል ከተስማሙበት ዋጋ ላይ ታሳቢ ይደረግላችኋል / ይቀነስላችኋል።
ሙሉ ዉክልና
![REPRESENTATION 3_edited_edited_edited_edited.jpg](https://static.wixstatic.com/media/7fc945_196cd6dfdf934aa2851e3930598fc3ca~mv2.jpg/v1/fill/w_329,h_210,al_c,lg_1,q_80,enc_avif,quality_auto/REPRESENTATION%203_edited_edited_edited_edited.jpg)
ለምክክር ኣገልግሎት ከሚመጡ ኣብዛኞቹ ደንበኞቻችን፥ ሁሉንም ያካተተ የተሟላ application package እንድናዘጋጅላቸው፥ ሒደቱን ተከታትለን እዳር እንድናደርስላቸው፡ ሙሉ ዉክልና ይሰጡናል። እኛ ደንበኞቻችን፥ በመንግስት እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸውን ኣስፈላጊ መስፈርቶች፥ ብዝርዝር በመግለጽ ስብሰባችንን እንጀምራለን። ከዚያ በኋላ፥ እንዲሟሉ የሚፈለጉት ሰነዶችን፥ ቅጾችና መረጃዎችን በመተንተን፥ ደንበኞቻችን ኣስፈላጊ የሆኑትን ፎርሞችን እንዲሞሉ እናግዛቸዋለን። ከዚህ በኋላ፥ ማመልከቻውን ለፊርማ ዝግጁ እናደርገዋለን። የብቃት/ጥራት ደረጃ (quality assurance) ለመጠበቅ እንዲያስችለን፥ የማመልከቻው ሙሉ ይዘት (application package) ዳግም የታየ/ የተመረመረ መሆኑን እናረጋግጣለን። እኛ የተሟላ ማመልከቻ ኣዘጋጅቶ መላክ፡ መለያችን እንዲሆን ነው የምንመኘው። በፎርሞቹ የሰፈረው መረጃን፥ መረጃውን የሚደግፉ ሰነዶችን ዳግም በመመርመር፥ የተሟላ ማመልከቻ በማቅረብ፥ የዳበረ ልምድ ኣካብተናል። ይኸንኑ፥ ለሙሉ የኣገልግሎት ውክልና (full representation service) የሚጠየቀው የኣገልግሎት ክፍያ፥ ኣብዛኛው ጊዜ ቀደም ሲል የዋጋ ተመን የወጣለት ሲሆን፥ የምክክር ስብሰባ እንደተካሔደ ወይም ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ፥ የሚወሰን ነው።
ማመልከቻው ወደ መንግስት ከተላከ በኋላ፥ እኛ የደንበኛችን ሕጋዊ ወኪል እንደመሆናችን መጠን፥ ማመልከቻውን ተቀብሎ ፥ ፕሮሰስ ከሚያደርገው፥ የካናዳ መንግስት ጽሕፈት ቤት ጋር፥ ግንኙነት እናካሒዳለን። ይኸን ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል ተብሎ ከተገመተው፥ ‘estimated processing time’ በላይ የወሰደ እንደሆነ፥ ድርጅታችን ፋይሉ የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅ ጽ/ቤቱን እንጠይቃለን። የዚህ ዓይነቱ ግንኙነት በምናካሒድበት ወቅት፥ እስከ ዛሬ ድረስ ከተለያዩ ኢምባሲዎችና የኢሚግረሽን ጽ/ ቤት ቅርንጫፎች እየተገናኘን፡ ከ12 ዓመታት በላይ ያዳበርነውን ሰከን ያለ ኣቀራረብ፡ ዲፕሎማሲያዊ ክህሎትና ልምድ በማዘውተር ነው። ተጨማሪ ሰነዶችን ለማቅረብ የተጠየቅን እንደሆነ፥ ባካበትነው ልምድና የሕግ ትምህርት ተመርኩዘን፥ የኢሚግረሽን ኦፊሰሩ በጉዳዩ ላይ ያለው ስጋት፡ ለማስወገድ በሚረዳ መልኩ፥ ኣሳማኝ የሕግ-ነክ ክርክሮች (legal arguments) በጽሑፍ ማቅረብ እንችላለን። ኣንድ ደንበኛ፥ ለኢንተርቪው የቀረበ እንደሆነ፥ ኣጋዥ ምክሮችን በመለገስ፥ ዝግጁ እንዲሆን እናደርጋለን። ሙሉ ውክልና ተቀብለን፥ ማመልከቻቸውን ስኬታማ እንዲሆን ያበቃናቸው ደንበኞች ቁጥር፥ ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ፥ እንኮራለን።
![TIME FOR REVIEW_edited_edited.jpg](https://static.wixstatic.com/media/7fc945_d1efa8f1bd5c4904ba490430c98ddcd6~mv2.jpg/v1/fill/w_363,h_272,al_c,lg_1,q_80,enc_avif,quality_auto/TIME%20FOR%20REVIEW_edited_edited.jpg)
ዳግም የማየት / የመመርመር ኣገልግሎት
እርስዎ ያዘጋጁትን ማመልከቻ application; ኣግባብ ባለው የስራ ልምድ በተካነ ባለ ሙያ፥ በጥንቃቄ የተመረመረ መሆኑን ለማወቅ መቻልዎ፥ የኣዕምሮ ዕረፍት ሊያስገኝልዎ ይችላል። ማመልከቻውን (ቅጾቹንና፥ እነዚህን የሚደግፉ ተያያዥ ሰነዶችን) እንመረምራለን። ማመልከቻ ቅጾች ላይ ያገኘናቸውን ግድፈቶችና ጉድለቶችን የሚያርመውን ምክር፥ በጽሑፍ እንሰጣለን። በቀረቡት ሰነዶች የብቃት ደረጃና ይዘት ላይ፥ ሓሳብ እንሰጣለን። ከዚህ በኋላ ታድያ፥ በደንበኞች በኩል የተዘጋጀውን ማመልከቻ (application package) ወደ ኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት የመላክና፥ ከዚያም ቀጥሎ ከጽሕፈት ቤቱ ጋር የሚካሔደው የጽሑፍ ልውውጥ ማድረጉ፥ የደንበኞቹ ሓላፊነት ይሆናል። ለማመልከቻው ዳግም መታየት / መመርመር የሚያስከፍለው መጠን ገንዘብ፥ በሚመለከተው የኢሚግረሽን ዘርፍ /ዓይነት ፥ ጉዳዩ የሚጠይቀው የስራ ክብደትና የውስብስነት ደረጃ፥ በማመልከቻ ዉስጥ የሚካተቱት ሰዎች ብዛትና በተዛማጅ ጉዳዮች ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል።